አሁን ያለንበት የግብርና እና የምግብ ፖሊሲያችንን ብንመለከት በዋነኝነት የሚያተኩረው ዲዳጃታላይዜሽንና የክላሰተር እርሻ ላይ ነው፡፡ ይህም በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የሚመራ ሲሆን በተለይ መከናይዜሽን እርሻ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው፡፡ በቅርቡ አንዳውም በግብርና ሚኒስቴርና አስተባባሪነት ሁሉም ዘርፎች ያሉበት 22 ስርነቀል ለውጥ የሚያመጡ መርሐ ግብሮች እየተተገበሩ ይገኛሱ፡፡

ጋዜጣ_ፕላስ፦ ኢትዮጵያ የምግብ ሱዓላዊነቷን ማረጋገጥ ያስችላት ዘንድ በርካታ የልማት መርሐ ግብሮችን ነድፋ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች ወዲህ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አያስመዘገበች ትገኛለች፡፡ በዋነኝነትም የሌማት ቱሩፋትና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ያመጣው ውጤት ዋቢ ሆነው ይጠቀሳሱ፡፡ በተለይም ከአርሻ እስከ ጉርሻ የሰውን የምግብ ሥርዓት ሰማዘመንና ለማሻሻል በተደረጉ ጥረቶች የምግብ ዋስትና ስጋት የነበረባቸው ጥቂት የማይባሉ ዜጎች ከተረጂነት ወደ አምራችነት መለወጥ ችለዋል፡፡ ይሁንና በየጊዜው እያደገ ካለው የሕዝብ ቁጥርና ፍላጎት አንፃር የሚመረተው ምርት ተመጣጣኝ ባለመሆኑ አሁንም በርካታ ዜጎች ከጠባቂነት መላቀቅ አልቻሱም።...
- https://press.et/am-stories/detail/4kb9s7xs7j1v4spdq33rhfj8d6
- https://press.et/am-stories/detail/4jkyhna5gb3zfvrgtf43dx3sw3